“እናቴ በተደጋጋሚ ሰው መሆኔ አይቀርም ትላለች፡፡ እኔንም ሰው መሆኔ እያለች ነበር የምትጠራኝ ፡ ይሀም በሂደት ሰው መሆን ሆነ፡፡ለእናቴ በጣም ልዩ ፍቅር አለኝ ፡ አሁን በህይወት ባይኖሩም ህልሟ በህይወት አለ ብዬ አምናለው ፡ የሷ ህልም እኔ የተሻለ ሰው እንድሆን ማድረግ ፡ ስኬታማ ሁኜ ማየት ነው ፡፡ የእናቴን ህልም ደግሞ ማኖር ነበረብኝ ፡ ለሱ ህልሟ ስል መታተሬ ፡ ለሱ ህልሟ ስል መጣሬ አሁን ያለሁበት ቦታ አድርሶኛል ብዬ አምናለው፡፡ “ የዛሬ እንግዳችን በጎንደር ከተማ ትንንሽዬ ፊልም ቤቶች የተጀመረው የዛሬ እንግዳችን የጥበብ ጉዞ ፡ ዛሬ ሀገራችን ላይ አሉ የተባሉ እንደ ፔንዱለም፤ሲቲ ቦይስ፤ ባላገሩ፡ ያልታሰበው ፤ ቀሚስ የለበስኩለት፡ የፀሀይ መውጫ ልጆች፡ አለሜ፡ እውር አሞራ ቀላቢ፡ሰውነቷ ፡የመሳሰሉ ፊልሞችን እንደ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር ፡ እንዲሁም ማር እስከ ጧፍ (ቴዲ አፍሮ) ፣ የዘፈን ማሞቂያ አይደለም (እሱባለው ) ጥቁር ሰው (ቴዲ አፍሮ) ፡ finally (Thabsi) የመሳሰሉ የሙዝቃ ክሊፖችን እስከ መስራት ደርሷል፡ በቅርብ የምናውቀውን አደይ ድራማ ፡ አሁን ደግሞ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያለውን ፍቅር እስከመቃብር መፅሀፍን ወደ ፊልምነት በመቀየር ላይ ይገኛል፡፡ Canon የካሜራ አምራች ድርጅት ሁለት ሽልማትን ሸልሞታል ፡ ከሳቢሳ ፕሮዳክሽን መስራቾች ውስጥም አንዱ ነው ፡፡ የሰው መሆን እና ዲስራፕተርስ ፊልም ድርጅት ባለቤትና መሪም ነው ፡፡ አቅራቢዎቻችን ከሰው መሆን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፡ የፊልም ኢንደስርሪያችንን ከ ጥፍር እስከ ጠጉሩ ግልብጥ አድርገው ተወያይተውበታል ፡ አሁን ወደ ኢንደስትሪው ለሚገቡ እና፡ ስለ እንደስትሪው ጥልቅ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለሚያስቡ ሰዎች ፡ የሚሆን ድንቅ ቆይታ ነው፡፡ ትልቅ የዋጋ ምንጭ እንደሚሆንላችሁ በማመን ፡ እንድትመለከቱት ጋበዝናችሁ ፡፡ መልካም ቆይታ ! በቻናላችን የሚለቀቁ ቪድዮዎችን ከሚመለከቱ ተከታታዮቻችን መሀከል ወደ ሰባ በመቶ የሚሆኑት ሰብስክራብ ያላደረጉን ናቸው፡፡ ይህን ቁጥርም ወደ 50 በመቶ ለማሳነስ አቅደን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ከምናቀርባቸው እንግዶች ጋር የሚኖረን ቆይታ፡ አንዳች ዋጋ ያለው ነገር እንደሰጠዎ ካመኑ ብቻ፡ ይህን ግባችንን ማሳካት እንድንችል ፡ ሰብስክራይብ በማድረግ እንዲተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን! #fikireskemekabir Social Links https://www.linkedin.com/company/meripodcast/ https://www.tiktok.com/@meripodcast https://twitter.com/MERI_Podcast https://www.instagram.com/meripodcast/ https://t.me/MERI_PODCAST https://youtube.com/@Meriwoch?si=yIpJ3byprnVNwKi1 Copyright Notice for Meri Podcast: All rights reserved. The content featured in this podcast is protected by copyright laws. Unauthorized reproduction, distribution, or modification of any portion of this podcast is strictly prohibited. For permission to use our content, please contact us at meripodcastet@gmail.com Thank you for respecting our copyright.