ሰላም እንዴት ቆያችሁን ውድ የመሪ ፖድካስት ተከታታዮቻችን፡፡ የዛሬው እንግዳችን ኢር. ዳዊት አብርሀምን ይባላል ፡፡ ኢር. ዳዊት ከ አ.አ ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የተመረቀ ሲሆን፡፡ የ 2ኛ አመት ተማሪ ሳለ የተዋወቀው የፕሮግራሚንግ ዘርፍ ላይ ባደረበት ልዩ ፍቅርም ፡ አብዛኛውን ግዜውን እንዲሰጠውን እና በዘርፉም ልቆ እንዲወጣ ሆኑዋል፡፡ ኢር. ዳዊት በግዜው በሀገራችን ብዙ ያልተለመደውን የጌሚንግ ኢንደስትሪ በመቀላቀል ፡ እንደ ኩኩሉ እና ገበጣ ያሉ ጨዋታዎችን ፡ እሱና የስራ አጋሮቹ ሁነው ባቋቋሙት ቅኔ ጌምስ ስር ሰርተው ለተጠቃሚዎች አብቅተዋል ፡፡ እንግዳችን ከ አቅራቢዎቻችን ጋር በነበረው ቆይታ አንድ ስታርታፕ እንዴት መጀመር እንዳለበት ቀጥሎም በምን አይነት መልኩ ራሱን ለ ኢንቨስትመንት ዝግጁ ማድረግ እንደሚቻል ፡ እንዲሁም አንድን ድርጅት መሸጥ ደረጃ ድረስ እስክናደርሰው የምናልፋቸውን የተለያዩ ሂደቶች አና ሌሎች ሀሳቦች በሰፊው ተወያይተዋል፡፡ አዲስ ቢዝነስ ለመጀመር እያሰባችሁ ያላችሁ ፡ የጀመራችሁ እንዲሁም ፡ ቢዝነሳችሁን አሳድጋችሁ ለመሸጥ ምታስቡ ተከታታዮቻችን ልታዩት የሚገባ ድንቅ ቆይታ ነው ፡ ተጋበዙልን፡፡ Social Links https://t.me/MERI_PODCAST https://twitter.com/MERI_Podcast https://www.instagram.com/meripodcast/ https://www.youtube.com/channel/UCzKNuQ80qNSpt2x-7dsazJg https://www.tiktok.com/@meripodcast https://www.linkedin.com/company/meriethiopian/